ሀገሬ ቲቪ

ስዊዝ ባንክ ከባድ የሚባል ኪሳራ እንዳጋጠመው ገለጸ

ስዊዝ ባንክ በ116 አመት ውስጥ ገጥሞት የማያቅ ከባድ ኪሳራ እንዳጋጠመው ገለጸ።

ባንኩ በፈረንጆቹ 2022 የበጀት አመት 132 ቢሊዮን የስዊዝ ፍራንክ ወይም 143 ቢሊዮን ዶላር የከሰረ ሲሆን ይህም በፈረንጆቹ 2022 ክብረወሰን የሰበረ ኪሳራ ነው ተብሏል።

ከዚህ ቀደም በፈረንጆቹ በ2015 የ23 ቢሊዮን የስዊዝ ፍራንክ ኪሳራ አጋጥሞት የነበረ ሲሆን የዚህ አመቱ ከሌሎቹ ጊዜያት አስደንጋጭ ቁጥር ነው ተብሏል።

በዮሴፍ ከበደ
2023-01-11