ሀገሬ ቲቪ

የአማዞን ባለቤት ጄፍ ቤዞስ የተወለደበት ቀን

በዓለማችን ቀዳሚ የበይነ መረብ መገበያያ እና የተለያዩ ድርጅቶች ባለቤት የሆኑት ጄፍሪ ፕሬስተን ቤዞስ ከ እናቱ ጃክሊን ጋይስና ከአባቱ ቴዲ ኦርገንስ የተወለደው ጥር አራት ቀን 1964 ዓ.ም በዛሬዋ ቀን ነው።

ቢዞስ በተወለደ በጥቂት አመታት እናት እና አባቱ ባለመግባባት ፍቺ የፈጸሙ ሲሆን ቤዞስ በለጋ እድሜው ከአባቱ ተልይቶ ከ እናቱ ጋር ማደግ ጀመረ ።

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በቴክሳስ ፤ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በፍሎሪዳ ተምሯል። ቤዞስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በሚማርበት ሰዐት የፈጠራ ሀሳብ ያላቸውን ተማሪዎች የሚያበረታታ ድሪም ኢኒስቲቲዩት የሚል ማዕከል በማቋቋም የተለያዩ ፈጠራዎችን አስገኝቷል።

የሀይስኩል ትምህርቱን በከፍተኛ ውጤት በማጠናቀም በ 1986 ከ ፕሪንትስተን ዩኒቨርሲቲ በኤሌክሪካል ኢንጂነሪንግ እና ኮምፒውተር ሳይንስ በከፍተኛ ማዕረግ ተመርቋል ።

ከዩኒቨርሲቲ በኋላ ከሁለት ድርጅቶች ውጪ ተቀጥሮ መስራት ያልፈለገው ጄፍ በ1995 ወደ ሲያትል በማምራት ከወላጆቹ በተበደረው 300ሺ ዶላር የመጀመሪያ የሆነውን የበይነ መረብ መጽሀፍ መሸጫ በመክፈት የዓለም ህዝብ ባሉበት ሆነው መጽሀፎችን እንዲገዙ አደረገ።

በመቀጠልም ከመጽሀፍቶች በተጨማሪ ኤሌክትሮኒክስ ፤ አልባሳት እንዲሁም የተለያዩ ዕቃዎች በድህረገጹ መሸጥ ጀመሩ ። ይህ ድርጅት አሁን ላይ የዓለማችንን የበይነ መረብ ግብይት የተቆጣጠረው አማዞን ነው።

በዚህ ያላበቃው ቱጃሩ ሰው በጎርጎሮሳዊያኑ አቆጣጠር 2000 ዓ.ም ወደ ጠፈር የመብረር ህልሙን ለማሳካት ይረዳው ዘንድ ብሉ ኦሪጅን የተሰኘ ድርጅት መሰረተ ።

በ2015 ዓ.ም የመጀመሪያው የሆነውን ሮኬት ወደ ሕዋ አመነጠቀ ። በአማዞን እንዲሁም በሌሎች ድርጅቶቹ ከቀን ወደ ቀን አያሌ ገቢዎችን እያገኘ የመጣው ጄፍ ቤዞስ በ2018 ዓ.ም የአለማችንን ቢሊየነሮች ደረጃ የሚያወጣው ፎርብስ መጽሄት የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለሀብት 112 ቢሊዮን ዶላር ያለው ጄፍ ቤዞስ ነው ሲል አወጀ ።

በፎርብስ የቢሊየነሮች ዝርዝር ባለፉት 24 ዓመታት ውስጥ 18 ጊዜ ቀዳሚ የነበሩት ቢል ጌትስ በ90 ቢሊዮን ዶላር የቤዞስ ተከታይ ሆኑ።

በ 2020ም በ 202 ቢሊዮን ዶላር ቤሶዝ የአንደኝነቱን ደረጃ አስጠብቋል ። ጄፍ ቤዞስ አሁን ላይ የዐለማችን ሁለተኛው ባለሀብት ሲሆኑ የቴስላና በቅርቡ ትዊተርን የግሉ ያደረገው ኤለን መስክ በአንደኝነት ተቀምጠዋል።

በዮሴፍ ከበደ
2023-01-12