ሀገሬ ቲቪ

ቅንጡዋ የዓለማችን መርከብ አደጋ የደረሰበት ዕለት

በ21ኛው ክፍለ ዘመን የተገነባች የዓለማችን ውዷ እና ቅንጡዋ መርከብ ናት ይሏታል፤ ኮስታ ኮንኮርዲያ።

የዛሬ አስራ አንድ አመት በዛሬዋ ዕለት መንገደኞችን አሳፍራ ስትጓዝ በጊግሊዮ ደሴት ከቋጥኝ ጋር በመጋጨቷ የ32 ሰዎች ህይወት አልፎ ነበር።

በዚህም መርከቧን ሲዘውራት የነበረው ካፒቴን ፍራንሲስኮ ሸቲኖ በአደጋው ተጠያቂ ተደርጎ ተከስሶም ነበር። የዕለቱን ከታሪክ ትኩረታችን ነው።

ዓለም ታሪኳን መዝግቦ ካስቀመጠላቸው ዝነኛ መዝናኛዎች አንዷ ታይታኒክ ናት። ይህቺው ቅንጡ የባህር ላይ መርከብ መጨረሻዋ ከበረዶ ግግር ጋር ተላትሞ ከባህር በታች መቀበር ሆነ እንጂ።

ይህኛውም ከዚያ የተለየ አይደለም ዓለም ለመዝናናት ሲል የሰራት የግዜው ቅንጡ የባህር ላይ መርከብ፣ ግዙፍ እና የወጣባት ገንዘብ ጭምር ያንስባታል የሚባልላት ፣ ውስጧ ኪሳቸው ለሞላ ከበርቴዎች እንጂ በቂ ገንዘብ ለሌላችው ሰዎች መዝናናትን ሳይሆን የጉልበት ስራን የምታቀርብ መርከብ ነች፤ የጣሊያኗ ኮስታ ኮንኮርዲያ። ባለቤትነቷም ኮስታ ክሮሲሬ የሚያስተዳደረው ካርኒቫል ኮርፖሬሽን ፒ ኤል ሲ ነው።

290 ሜትር ርዝመት እና 3780 መንገደኞችን የመጫን አቅም ያላት ሲሆን ውስጧም የተለያዩ ቅንጡ የመዝናኛ ስፍራዎች፣ ስፓዎች፣ እና ትላልቅ የመዋኛ ገንዳዎች አሏት።

በዛሬዋ እለት በ2004 ዓ.ም ኮስታ ኮንኮርዲያ ከጣሊያን ከምሽቱ 01፡20 ሲሆን 3,206 ተሳፋሪዎን እንዲሁም 1,023 የመርከብ ሰራተኞችን ጭና ከሰዓታት በኋላ ጊግሊዮ ደሴት ላይ ደረሱ።

ደሴቱ በበርካታ ቋጥኞች የተሞላ ነበር ይህንንም በጉዟቸው ውቅት እያስተዋሉት አልፈዋል። መርከቧንን ሲዘውራት የነበረው ኢንዲኔዥያዊ ካፒቴን በቋንቋ አለመግባባት ምክኒያት መርከቧ በተቃራኒ አቅጣጫ እንድትጓዝ አደረገ።

በተሳሳተ አቅጣጫም እንደተጓዙ ለመረዳት ብዙ ጊዜ አልፈጀባቸውም ነበር። እንደገና የመርከቧም አቅጣጫ አስተካክለው መጓዝ ጀመሩ ከምሽቱ 3፡45 ሲሆን መርከቧ ከቋጥኝ ጋር ተጋጨች፡፡

መርከቧ በግራ በኩል 53 ሜትር ያህል ተጎዳች። የሞተር ክፍሏን ጨምሮ ሌሎች አምስት ክፍሎች በውሃ ተጥለቀለቁ። ከደቂቃዎች በኋላ ደግሞ መርከቧ ብርሃኗን አጣች፡፡

በዚህም መርከቧ ሞተሯም ሆኑ መቅዘፊያዎቿ ስለማይሰሩ ምንም ነገር መቆጣጠር አልቻሉም ነበር። ይሁን እንጂ የንፋሱ እና የመቅዘፊያው አቀማመጥ ኮንጆርዲያ ወደ ደሴቱ አቅጣጫ እንድትመለስ አደረጓት።

በዚህን ጊዜ በጭንቀት ተውጠው ከነበሩት ተሳፊሪዎች መካከል አንዷ ለልጇ ደውላ ስለሁኔታው ትነግራታለች። በጣሊያን ለሚገኙ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎችም ወደ መርከቧ ካፒቴን ሲቲኖ ደወሉ።

ነገር ግን ጉዳቱን ቀለል አድርጎ ነበር የነገራችው። ከ10 ደቂቃዎች በኋላ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎቹ ደወሉ ካፒቴኖቹም መርከቧ በመስመጥ ላይ እንዳሉ ተናገሩ።

ከዚህ በኋላ ነበር 25 ተጠባባቂ የነፍስ አድን መርከቦች 14 የንግድ መርከቦች እና በርካታ ሄሊኮፍተሮች በኮንካርዲያ ተሳፍረው የነበሩ መንገደኞችን እና ሰራተኞችን ነፍስ ለማዳን የተሰማሩት። ከአደጋውም 4194 ሰዎችን በህይወት ማትረፍ የቻሉ ሲሆን 32 ሰዎች ደግሞ በህይወት ሳይሆን በድናቸውን አገኙ።

ለአደጋውም ኮስታ ኮንኮርዲያን ሲዘውራት የነበረው ካፒቴን ፍራንሲስኮ ሺቲኖ ተጠያቂ በመሆን ክስ ተመሰረተበት። አደጋው ከታይታኒክ መስመጥ በኋላ በትልቅ የመዝናኛ መቅንጡ መርከብ ላይ የደረሰ አደጋ በሚል ተመዘግቧል።

በማህሌት አማረ
2023-01-13