
የዓለማችን ቀዳሚ አንድ በመቶ ባለሀብቶች ከዓለማችን 42 ትሪሊየን ዶላር ሀብት ሁለት ሶስተኛውን እንደሚይዙ ኦክስፋም አስታወቀ።
ኦክስፋም ይህንን ያስታወቀው በዓመታዊው የዓለም አቀፉ የኢኮኖሚ ፎረም ላይ ነው። የ አንድ በመቶዎቹ ባለሀብት አጠቃላይ የሀብት መጠን ከ99 በመቶው ዝቅተኛው የዓለም ህዝብ እጥፍ ያክል ማለት እንደሆነም ጠቁሟል።
የቢሊየነሮቹ ሀብት በየቀኑ በአማካይ በ2.7 ቢሊዮን ዶላር እየጨመረ ሲሆን በትንሹ 1.7 ቢሊዮን የሚደርሱ ሰራተኞች ግን ከደመወዛቸው ጋር ግብግብ ከገጠመው የዋጋ ንረት ጋር እየታገሉ መሆኑንም ገልጿል።
በአብርሃም በለጠ
2023-01-16