ሀገሬ ቲቪ

ኮሎኔል ጋዳፊ ሊቢያን በፕሬዘዳንትነት መምራት የጀመሩበት ቀን

ኮሎኔል ሙአመር ጋዳፊ ሊቢያ ጠንካራ ሃገር እንድትሆንም በብዙ ደክመዋል ። ለዜጎቻቻው የተሻለ ኑሮን መስጠትም ችለዋል።

ኮሎኔል ሙአመር ጋዳፊ በንጉስ ኢድሪስ ላይ የመፈንቅለ መንግስት ካደርጉ ከ4 ወራት በኋላ በዛሬው ቀን ከ53 አመት በፊት ነበር የሊቢያ ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት ። የእለቱን ከታሪክ ትኩረታችን ነው።

በአፍሪካ የመሪዎች ታሪክ ወስጥ ሰማቸው ሳይጠቀስ አያልፍም ። ኮስታራ ፣ቆራጥ እና ደፋር መሪም ናቸው ። በመድረኮች ላይ ቆሞ ሲያወሩ ሰውን የመሳብ አቅም አላቸው ።

የሊቢያ አባት የፓን አፍሪካኒዝም አቀንቃኝም ናቸው ኮሎኒል ሙአመር አል ጋዳፊ ። የተወለዱት በ1934 በሊቢያ ሲርጥ ከተማ ወስጥ ነው ። ጋዳፊ በትምህርታቸው ጎበዝ የሚባሉ ተማሪ ናቸው ።

በትምህርት ጎበዝ የነበሩት ጋዳፊ በሊቢያ ቤናጋዚ ዩኒቨርሲቲ ወስጥ ገበተው የታሪክ ትምህርትን አጥንተዋል ። በ1950ዎቹ አጋማሽም የጦር ትምህርትን በሊቢያ የጦር አካዳሚ ተገኝተው ትምህርትን ቀሰመዋል ።

ሊቢያ ከቀኝ ገዥዎቿ ጣሊያን እና እንግሊዝ ነጻ ከወጣች በኋላ ትመራ የነበርው በንጉስ እዲሪስ ስረወ መንገስት ነበር ።ንጉስ እድሪስ በነበራቸው አመራራ በሊቢያውያን ዘንድ ተወዳጅ አልነበሩም ለዚህም ምክንያት የነበረው ንጉስ እድሪስ ከተቀሩ የአረብ ሃገራት ያላቸው ግንኙነት አመርቂ ያልሆነ እና ለዝብ ማለት በብዙ ሊቢያውያን ዘንድ ተወዳጅ እንዳይሆኑ አድርጓቸዋል ።

ታዲያ ይህ አገዛዝ መለወጥ አለበት በለው በህዝቡ ዘንድ የነበረውን የለውጥ ፍላጎት የሊቢያው የጦር አካዳሚ ምሩቁ ኮሎኔል ሙአመር ጋዳፊ ተቀላቀሉ ። በህዝቡ ዘንድ የነበረው የለወጥ አቢዮት ፈንደቶ በመስከረም 1 1962 ዐ.ም ላይ ያለምንም የደም መፋሰስ የመፍንቀለ መንግስት ተከናወነ ።

ኮሎኔል ሙአመር ጋዳፊ የዚህ አቢዮት መሪም ነበሩ ። ንጉስ እድሪስ ለህክምና ወደ ቱርክ እንዳቀኑ በዛው ቀሩ ። ይህ ክስተተ ለሊቢያወያን አዲስ ምዕራፍን ከፈተ ።

በሊቢያ ግዚያዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ሆነው የተሾሙት ኮሎኔል ሙአመር ጋዳፊ ከአራት ወራት በኋላ በዛሬው ቀን ከ 53 አመት በፊት በሊቢያ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ ።

ሙአመር ጋዳፊ ከዚህ በኋላ የሶሻሊዝም ፣ ጠንካራ የእስላምዊ መንግስትን በማቋቋም ሊቢያን መመራት ጀመሩ ። ጋዳፊ በስልጣናቸው መጀምሪያ በሊቢያ የሚገኙ የጣሊያን እና የእንግሊዝ የጦር ሰፈሮችን ወደ መንግስታቸው ጠቅልለው ወታደሮቹን ከሊቢያ አስወጥተዋል ።

በምዕራባዊያን ተይዘው የነበሩ የሊቢያ የነዳጅ ተቋማትን ለመንግስታቸው ገቢ አድርገዋል ። ሊቢያዊያን በጋዳፊ ዘመን በርካታ የኑሮ ማሻሻያዎችን አግኘተዋል ። ነጻ የትምህርት እድል ፣ የነጻ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ አድረገዋል ።

ጋዳፊ ጠንካራ የአረብ ብሄርተኛ አቀንቃኝ በመሆናቸው ከተለያዩ የአረብ ሃገራት ጥምረትን ለመመስረት ሞክረዋል ። አፍሪካም አንድ ሆና በተቀረው አለም ጠንካራ እንደትሆን ተደጋጋሚ ጥሪን አቅረበዋል ።

በምዕራቡ አለም ጥርስ የተነከስባቸው ጋዳፊ በ አረብ ሃገራት የተቀጣጠለው የለውጥ አብዮት ስልጣንቸውን ነቀነቀው ።

በሊቢያ የእርስ በአርስ ግጭት በረከት ። ጋዳፊም አምጽ እና ተቃውሞ በርክቶ ቤትመንግስት በር ላይ ሲደርስ ለመሸሸ ሞከሩ ባይሳካም ። በመጨረሻም በአንድ የውሃ መውረጃ ትቦ ወስጥ ተደብቀው የተገኙት ጋዳፊ በሞት ቅጣት ተፈረዳባቸው ።

ከዚህ በኋላ በስልጣን ጥም የሰክሩ የራሷ ልጆች የበረሃ ገነት የነበረችው ሊቢያ ወደ ፍርስራሽነት ቀየሯት ። ይመጣል የተባለው ለውጥ የውሃ ሽታ ሆኖ ቀረ ዛሬም ሊቢያ ከጋዳፊ በኋላ ሰላም እንደራቃት አለች።

በወንድምአገኝ አበበ
2023-01-16