
አፍሪካ ለጆሮ የከበዱ፣ ሰውነትን ወዲያ የሚያሰኙ የሰቆቃ ግዜያትን ህዝቦቿ አሳልፈዋል።
በተፈጥሮ ሀብት ቀዳሚ የሌላት አህጉርን እግረ ደረቅ ያሰኙ መሪዎች ህዝቦቿን ሞት ወዴት አለህ አሰኝተውታል።
ለክፉ መሪዎች ደረጃ ይውጣ ቢባል ከቀዳሚዎች ውስጥ የማይታጡም ናቸው ይባልላቸዋል። ፊልድ ማርሻል ኤዲያሚን ዳዳ።
እንዲያው እንዲቀለን ብለን እንዲህ ጠራነው እንጂ የኢዲያሚን ስም እንዲሁ የሚዘለቅ አይደለም።
አንድ ሰው እሱን ሲጠራ “የተከበሩ የህይወት ዘመን ፕረዚዳንት፣ ፊልድ ማርሻል፣ አል ሃጂ፣ ዶክተር ኢዲ አሚን ዳዳ የቪሲ፣ የዲኤስኦ፣ የኤምሲ መሪ፣ የምድር አራዊት እና የባህር ዓሳዎች ጌታ እንዲሁም በአፍሪካ የብሪቲሽ ኢምፓየር በተለይም በኡጋንዳ ጠቅላይ። ብሎ መጥራት ግድ ነው። ይህንን ያላለ መጨረሻው ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት ከባድ ነው።
ኤድያሚን ዳዳ መቼ ተወለደ፤ በርካቶችን የሚያነጋግር ነው፤ አንዳንዶች በ1918 ተወልዷል ይላሉ። በ1916 የሚሉም አሉ።
ቤተሰቦቹ በመለያየታቸው ሳቢያ ገና በልጅነት ድሜው ስራ እየሰራ ለመኖር መገደዱን እራሱ ተናገረ እንጂ ስለልጅነት ሕይወቱ ከዚህ በላይ የሚያውቅ ማንም የለም።
ጥቂት ዓመታትን ብቻ መደበኛ ትምህርት ከተማረ በኋላ በ1938 ወታደር ቤት መቀላቀሉን እራሱ ይናገራል።
በእንግሊዞች የግፍ ቀንበር ስር የነበረችዋ ሀገር ዩጋንዳ በመስከረም 1955 ዓ.ም ነፃነቷን አገኘች።
ሚልተን ኦቦቴ የሀገሪቱ የመጀመሪያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ። ኤዲያሚንንም የጦራቸው መሪ አድርገው መረጡት።
ይህ የአቦቴ ውሳኔ ኝ ኋላ መዘዝን ይዞባቸው መጣ ያልተሳካ የግድያ ሙከራ ተደረገባቸው፤ ኣኤዲያሚንን ታማኝነት መጠራጠር የጀመሩት አቢቴ ለኮመን ዊልዝ የመሪዎች ስብሰባ ሲንጋፑር በሄደበት እንዲታሰር አዘዙ።
ኤዲያሚን ዳዳ ግን ባሌለበት በአቡቶ ላይ መፈንቅለ መንግስት አደረገ፤ ተሳካለትም። የዩጋንዳውያን የቅዠት ቀን አንድ ብሎ የዛኔ መቁጠር ጀመረ።
ጥር 17 1963 ዓ.ም. የዩጋምንዳን መንግስት ፈንቅሎ የሀገሪቱ መሪ አድርጎ እራሱን ሾመ።
ኤዲያሚን ዳዳ ከ1963 እስከ 1971 በቆየባቸው 8 የስልጣን ዓመታት ዜጎቹን በማሰቃየት የመራ በሚል በአንባገነንነት ይጠቀሳል።
ኤዲያሚን ስልጣን በጨበጠ ማግስት የአቦቴ ታማኝ በነበሩ ደጋፊዎቻቸው እና በአቾሊ እና ላንጎ በተባሉ የክርስትና እምነት በሚከተሉ ጎሳዎች ላይ የጅምላ ጭፍጨፋን አድርጓል።
በ1964 ዓ.ም፤ መንግስት ገልብጦ ስልጣን በያዘ ማግስት ማለት ነው፤ ከ50 እስከ 70 ሺሕ የሚጠጉ ዩጋንዳ ኤዢያውያንን ከሀገሩ አባሯል።
በሰኔ ወር 1968 ዓ.ም. ከእስራኤል ወደ ፓሪስ የሚሄድ የፈረንሳይን አውሮፕላን የጠለፉትን የፍልስጤም ነፃ አውጪ ህዝባዊ ግንባር ሰዎችን በኢንቴቤ እንዲያርፉ ፈቃድ ሰጠ።
ኋላም በእስራኤል የስለላ ተቋም ጥረት ከዩጋንዳው ኢንቴቤ አየር ማረፊያ ታጋቾቹን ማስለቀቅ ተቻለ።
በዚህ የተበሳጨው ኤዲያሚን ዳዳም ከእስራኤሎች ጋር አብረዋል ያላቸውን የአየር መንገዱን ሰራተኞች እንዲረሸኑ አደረገ።
ኤዲያሚን ከእስራኤል፣ አሜሪካን ጨምሮ እዚህ ያደረሰችውን እንግሊዝን ጭምር ወደ ጎን በማለት ፍልስጤምን ከመሰሉ ሙስሊም ሀገራት ጋር ተወዳጅቷል።
በኤዲያሚን የስልጣን ዘመን 300 ሺሕ የሚጠጉ ዩጋንዳውያን በጨካኝ መዳፋቸው መገደላቸው ይነገራል።
የኢድያሚን ከሀገራቸው ዜጎች አልፈው ታንዛኒያ ዜጎቼን እያሸሸችብኝ ነው ሲል በ1970 ዓ.ም. ጦርነትን አወጀባጥት።
የታንዛኒያው ፕሬዚዳንት ጁሊየስ ኔሬሬም በእብሪተኛው ኤዲያሚን የተወሰዱባቸውን ግዛቶች ለመመለስ የአፀፋ ምላሽን አዘዙ።
የታንዛኒያ ወታደሮች ከዩጋንዳ ብሔርተኞች ጋር በመተባበር ኤዲያሚን ዳዳን ተፋለሙጡ።
በሚያዛ 3 1971 ዓ.ም. በዩጋንዳ ብሔርተኞች የታገዘው የታንዛኒያ ጦር ካምፓላ ተቃረበ ኤዲያሚን ዳዳም ሀገር ጥለው ሸሹ።
በመጀመሪያ በሊቢያ ኋላም ወደ ሳውድ አረቢያ በማቅናት በስደት ኖሮ በ1995 ዓ.ም በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ህመም ሳቢያ መሞቱ ተሰምቷል።
የዛሬ 52 ዓመት በወርሀ ጥር 1963 ዓ.ም. በዛሬዋ ዕለት አምባገነኑ የሩጋንዳ ፕሬዚዳንት ኤዲያሚን ዳዳ መፈንቅለ መንግስት በማድረግ ስልጣን ያዙ።
በሳምሶን ገድሉ
2023-01-25