ሀገሬ ቲቪ

በዘንድሮ በጀት ዓመት በ10 ወራት ውስጥ ከአበባ፣ አትክልት እና ፍራፍሬ ዘርፍ ከግማሽ ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱ ተገለፀ።

በዘንድሮ በጀት ዓመት በ10 ወራት ውስጥ ከአበባ፣ አትክልት እና ፍራፍሬ ዘርፍ ከግማሽ ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱ ተገለፀ።

የአበባ ምርትን ወደ ውጪ በመላክ ከ493 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል።

97 ሺህ 296 ቶን የአበባ ምርት የተላከ ሲሆን፤ 145 ሺህ 330 ቶን የአትክልት እና ፍራፍሬ ምርቶችን ወደ ተለያዩ ሀገሮች ተልኳል።

በዚህም ከ 81 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጪ ምንዛሬ ማግኘት መቻሉን የኢትዮጵያ አበባ፣ አትክልት እና ፍራፍሬ አምራችና ላኪዎች ማህበር ለጣቢያችን ገልጿል።

በጥቅሉ ከዘርፉ ከግማሽ ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን ማህበሩ ጨምሮ አስታውቋል።

በሙሉጌታ በላይ
2023-05-30