ሀገሬ ቲቪ

የሰኔ ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ወደ 29 በመቶ ዝቅ ማለቱ ተነገረ፡፡

የሰኔ ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ወደ 29 በመቶ ዝቅ ማለቱ ተነገረ፡፡

የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት በመላው አገሪቱ የሚገኙ 119 የተመረጡ የገበያ ቦታዎችን መሠረት አድርጎ ይፋ በሚያደርገው የሸማቾች ዋጋ መመዘኛ ኢንዴክስ በሰኔ ወር ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሶች የዋጋ ግሽበት 31.4 በመቶ መድረሱንም አስታውቋል፡፡

የሰኔ ወር ዓመታዊ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 29.3 ከመቶ ሆኖ የተመዘገበ መሆኑ ሲገለጽ በግንቦት ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 30.8 በመቶ እንደነበር በ2015 የበጀት ዓመት አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት በአማካይ በየወሩ 2.2 በመቶ ይጨምር እንደነበረ ሪፖርቱ ያሳያል፡፡

ምንም እንኳን በአኃዝ ደረጃ የሚመዘገበው የዋጋ ግሽበት ባለፉት ሁለትና ሦስት ወራት መጠነኛ ቅናሽ እየታየበት መሆኑን የሚገልጽ ሪፖርት ይፋ ቢደረግም፣ አሁንም ውስን በሆኑ የምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሶች ላይ ተለዋዋጭ ሆኖ ከሚታየው መጠነኛ የዋጋ ቅናሽ በስተቀር በተለይም ምግብ ነክ ያልሆኑ ክፍሎች የዋጋ ጭማሪ እያገረሸ መሆኑን ሪፖርተር ያነጋገራቸው ሸማቾች ተናግረዋል፡፡

በብሩክታዊት አስራት
2023-07-17