ሀገሬ ቲቪ

ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ 75.8 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ 75.8 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡

ይህን ያስታወቀው የየ2015 ዓመት የበጀት መዝጊያን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ላይ ነው፡፡

ዘንድሮ የተገኘው ገቢው ካለፍው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ23.5 በመቶ እድገት ያሳየ መሆኑን የተቋሙ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ አስታውቀዋል፡፡

ከተገኘው ገቢ በዋናነት ከ43 በመቶ የድምፅ፣ 26 በመቶ የዳታ ኢንተርኔት እና 9 በመቶ የአለም አቀፍ ጥሪ ይሸፍኛሉ ተብሏል፡፡

9.5 ሚሊየን አዳዲስ ደንበኞችን ማፍራት የቻለ መሆኑም ተነስቷል፡፡

በተያዘው ዓመት 164 ከተሞችን የ4G ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት 300 ከተሞች የ4G ተጠቃሚ መሆናቸውን ስራ አስፈፃሚዋ ተናግረዋል፡፡

በወንድማገኝ አበበ
2023-07-18