ሀገሬ ቲቪ

ከቡና የወጪ ንግድ ከአንድ ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል

በ2015 በጀት ዓመት ከቡና የወጪ ንግድ ከአንድ ነጥብ ሦስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

በ2015 በጀት ዓመት 360 ሺህ 144 ቶን ቡና በላይ በመላክ አንድ ነጥብ 8 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 240 ሺህ 369 ቶን በላይ ቡና በመላክ ከአንድ ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘት ተችሏል፡፡ ይህም የዕቅዱን 67 በመቶ ማሳካት ተችሏል፡፡

በበጀት ዓመቱ የተላከው ቡና መዳረሻ ሀገራት መካከል ሳዑዲ ዓረቢያ፣ ጀርመን፣ አሜሪካ ለተገኘው ገቢ ትልቁን ድርሻ የሚይዙ ናቸው፡፡

በ2014 በጀት ዓመት 300 ሺህ ቶን ቡና ወደ ውጭ በመላክ ከአንድ ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱ ይታወሳል፡፡

በብሩክታዊት አስራት
2023-07-24