
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እግር ኳስን ለ22 ዓመታት በመጫወት ብቸኛው እግር ኳስ ተጫዋች የነበረው እና እግር ኳስ በቃኝ ያለው ደጉ ደበበ ከሀገሬ ስፖርት ጋር ቆይታ አድርጓል።
በነበረው ቆይታ “ወጣት ተጨዋቾች በስነ ምግባር መታገዝ አለባቸው፤ እግር ኳስን እንደ ሙያቸው ቆጥረው መስራት አለባቸው ሲል ተናግሯል፡፡
ደጉ ካነሳቸው ነጥቦች መካከል፦
“በእርግጠኝነት አርባ ምንጭ ከተማን በሚቀጥለው ዓመት በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ታዩታላችሁ”
“የግዜ ጉዳይ ነው በቅርቡ አሰልጣኝ ሆኜ እመጣለሁ”
“ወጣቱ እግር ኳስን ለብዙ ዓመት መጫወት ከፈለገ ስነ ምግባር ሊኖረው ይገባል”
“እኔን በክብር ለመሸኘት እንቅስቃሴ ተጀምሯል” እና ሙሉ ቆይታውን በምሽቱ የስፖርት ዜናዎቻችን ይጠብቁን፡፡
በይገደብ ዓባይ
2024-02-01