የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ዋና ኮሚሽነር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መራዘሙ አሳሳቢ ነው አሉ።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ከስድስት ወራት በፊት የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መራዘሙ አሳሳቢ ነው ሲሉ አስታወቁ።
ኮሚሽነሩ ይህን ያሉት አዋጁ መራዘሙ በሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ላይ ሊያስከትል የሚችለው አሉታዊ ተጽእኖ አሳሳቢ መሆኑን በማንሳት ነው።
ኮሚሽነሩ “የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አስፈላጊነት፣ ሕጋዊነት እና ተመጣጣኝነትን በአግባቡ ማጤን ይኖርበታል” ሲሉ በኤክስ ገፃቸው አስፍረዋል።
ኮሚሽነሩ አክለውም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲደነገግ ላስገደደው ችግር ውይይት ቁልፍ መፍትሄ ነው ሲሉ መክረዋል።
በናርዶስ ታምራት
2024-02-02