ሀገሬ ቲቪ

በኢትዮጵያ በረሃብ ምክንያት አንድም ሰው አልሞተም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።

በኢትዮጵያ በረሃብ ምክንያት አንድም ሰው አልሞተም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ዛሬ በተካሄደው 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስት አንዳንዶች ያሏቸውና በስም ያልጠቀሷቸው አካላት ‹‹ከ77ቱ ያልተናነሰ ድርቅ አለ›› የሚሉትን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በማብራሪያቸው በርሃብ ምክንያት በኢትዮጵያ አንድም ሰው አልሞተም ብሏል፡፡

ከቀናት በፊት የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በአማራና ትግራይ ክልሎች ዳሰሳ ባደረገባቸው አካባቢዎች ብቻ በድምሩ 372 ሰዎች በድርቁ ምክንያት መሞታቸውን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

በብሩክታዊት አሥራት
2024-02-06