ሀገሬ ቲቪ

በሰሜኑ ኢትዮጵያ ክፍል የተከሰተው ሰብአዊ ቀውስ እየጨመረ መምጣቱ ተነገረ።

በሰሜኑ ኢትዮጵያ ክፍል የተከሰተው ሰብአዊ ቀውስ እየጨመረ መምጣቱ ተነገረ።

የእንግሊዝ የአፍሪካ ሚኒስትር የሆኑት አንድሪው ሚሼል ለሁለት ቀናት በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ባደረጉት ወቅት በሰሜኑ የሀገሪቷ ክፍል የተከሰተው ሰብአዊ ቀውስ እየጨመረ መምጣቱን እንዳሳሰባቸው ተናግረዋል፡፡

ሚሼል በኢትዮጵያ ጉዟቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር በአዲስ አበባ ተገናኝተው መምከራቸው የተጠቆመ ሲሆን ወደ ትግራይ ክልል ርዕሰ መዲና መቀሌ ተጉዘው በክልሉ ጉብኝት ማድረጋቸው ተጠቁሟል።

ሚሼል በመግለጫቸው ላይ አለም በጋዛ ባለው ሰብዓዊ ቀውስ ላይ ተጠምዷል ያሉ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ያለው ሰብዓዊ ቀውስ የአለምን ትኩረት የሚሻ ነው ብለዋል ሲል ዘጋርዲያን ዘግቧል፡፡

በሰሜን ኢትዮጵያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ለረሃብ መጋለጣቸውን ጠቁመዋል፡፡

በናርዶስ ታምራት
2024-02-06