ሀገሬ ቲቪ

በኢትዮጵያ ከ900 ሺህ በላይ ስደተኞች እንደሚገኙ ተገለፀ።

በኢትዮጵያ ከ900 ሺህ በላይ ስደተኞች እንደሚገኙ ተገለፀ።

በኢትዮጵያ ከ26 ሀገራት የመጡ ከ900 ሺህ በላይ ስደተኞች እንደሚገኙ የስደተኞች እና ተመላሾች አገልግሎት ገለጸ።

በዚህም ከአፍሪካ ከኡጋንዳ እና ሱዳን ቀጥሎ በሶስተኛነት ደረጃ እንደምትገኝ ተመላክቷል።

አሁን ላይ በቀጠናው የሚገኙ ሀገራት ያለው ግጭት በሀገሪቱ የሚገኙ ስደተኞች ቁጥር እንዲጨምር ምክንያት መሆኑን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን ገልፀዋል።

በዚህም ኢትዮጵያ ስደተኞችን የመቀበል አቅሟ ጫና ውስጥ በመግባቱ አለም አቀፍ ድጋፍ ቢያስፈልጋትም በአለም አቀፍ ደረጃ ባለው ቀውስ ምክንያት ድጋፉ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ ተነስቷል።

ይህን ለመፍታትም ወደ ሀገራቸው የሚመለሱበት ሁኔታ ማመቻቸት እንዲሁም ስራዎችን እንዲሰሩና ራሳቸውን እንዲደግፉ እየተደረገ ነው ተብሏል።

በፂዮን ታደሰ
2024-02-06