ሀገሬ ቲቪ

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ 117 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ብድር ሰጥቻለሁ አለ።

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ 117 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ብድር ሰጥቻለሁ አለ።

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የግል የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢው ሳፋሪኮም፤ ‘’ኤም ፔሳ’’ በተሰኘ የፋይናንስ አገልግሎት በሚሰጠው መተግበሪያው አማካኝነት 117.5 ሚሊዮን ዶላር ብድር ለኢትዮጵያውያን ደንበኞቹ ማቅረቡን ዘኢስት አፍሪካ ዘግቧል።

ኩባንያው በዘጠኝ ወራት በቴሌኮም አገልግሎቶች ብቻ 30 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱንም አስታውቋል።

ይህ ገቢ የተገኘው እስከ ተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2023 መኾኑ ተገልጿል።

አሁን ላይ በኢትዮጵያ የኤምፔሳ ገንዘብ ዝውውር መጠን 115.6 ሚሊዮን ዶላር ሲደርስ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ቁጥርም 3.1 ሚሊዮን መድረሱ ተሰምቷል።

በሙሉጌታ በላይ
2024-02-07