ሀገሬ ቲቪ

በፓላንድ በተካሄደው ኦርሊን ኮፐርኒከስ ካፕ የቤት ውስጥ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች ድል ማድረግ ችለዋል፡፡

በፓላንድ በተካሄደው ኦርሊን ኮፐርኒከስ ካፕ የቤት ውስጥ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች ድል ማድረግ ችለዋል፡፡

ትናንት ምሽት በፖላንድ በተካሄደ የቤት ውስጥ ውድድር በ1500 ሜትር ኢትዮጵያዊው ሳሙኤል ተፈራ በ3፡34.61 በመጨረስ አሸንፏል፡፡

ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ቢኒያም መሃረይ በ3፡34.83 ሁለተኛ ሲወጣ በተጨማሪም የአለም ከ20 ዓመት በታች ክብረ ወሰንን አሻሽሏል፡፡

ሰለሞን ባረጋ በ3000 ሜትር ማሸነፍ ሲችል የራሱን ክብረ ወሰን በማሻሻል የዓመቱን ፈጣን ሰዓት አስመዝግቧል፡፡ በሴቶች 1500 ሜትር ፍሬወይኒ ኃይሉ በ3:55.28 የዓመቱን ፈጣን ሰዓት እና የ1500 ሜትር ሶስተኛ ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አሸንፋለች፡፡

ፍሬወይኒን በመከተል ኢትዮጵያውያኖቹ ድርቤ ወልተጂ፣ ሂሩት መሸሻ እና ትዕግስት ግርማ ከ2 እስከ 4 ያለውን ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል፡፡

በሴቶች 800 ሜትር ደግሞ ኢትዮጵያዊቷ ሃብታም አለሙ በ1:57.86 የዓመቱን ፈጣን ሰዓት በመያዝ አሸንፋለች፡፡

የሀገሯ ልጅ ወርቅነሽ መለሰ ለግሏ ምርጥ ሰዓት በሆነው 1:59.93 ሁለተኛ ወጥታለች፡፡

በይገደብ ዓባይ
2024-02-07