ሀገሬ ቲቪ

አዲስ አበባ ከተማ የአየር ብክለት ካስተናገዱ ከተሞች በ6ተኛ ደረጃ ላይ ተቀመጠች።

አዲስ አበባ ከተማ የአየር ብክለት ካስተናገዱ ከተሞች በ6ተኛ ደረጃ ላይ ተቀመጠች።

አዲስ አበባ ከተማ በአፍሪካ ከፍተኛ የአየር ብክለት ካስመዘገቡ ከተሞች ውስጥ በ6ተኛ ደረጃ መቀመጧን ቢስነስ ደይሊ ዘግቧል።

የአፍሪካ ከተሞች የአየር ብክለትን ይዞ በወጣው ዘገባ፤ የከተማዋ የአየር ብክለት መጠን መለኪያ 76.1 እንደሆነ ጠቁሟል።

ይህም ከ0 እስከ 50 በሚመዘገበው እና ጥሩ ከሚባለው በላይ ነው ተብሏል።

የከተሞች መስፋት፣ የኢንዱስትሪዎች መጨመር ለአፍሪካ ከተሞች የአየር መበከል ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።

የግብጿ ካይሮ 90.9 የአየር ብክለት መጠን አስመዝግባ በሰንጠረዡ ከላይ ተቀምጣለች።

በማህሌት አማረ
2024-02-07