
የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ድጋፍ እያቀረብኩኝ ነው አለ።
የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ በድርቅ እና በግጭት ለተጎዱ አካባቢዎች አስፈላጊ የምግብ እርዳታን እያቀረብኩኝ ነው አለ።
ተቋሙ በሰሜን ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናው እያሽቆለቆለ መምጣቱን እና ብዙዎች ለከፍተኛ ረሃብ እየተጋለጡ መሆናቸው እንዳሳሰበውም ጨምሮ ገልጿል።
ተቋሙ እስካሁን በአፋር፣ በአማራ፣ በትግራይ እና በሶማሌ ክልሎች ውስጥ 6.2 ሚሊዮን የሚጠጉ ከፍተኛ ጉዳት የገጠማቸው እና አስቸኳይ እርዳታ የሚሹ ሰዎችን በዲጂታል መመዝገቡን አስታውቋል።
በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በተከሰተው ረሃብ “በሽታን ለመከላከል” ለሦስት ሚሊዮን ሰዎች የነፍስ አድን እርዳታ ለማድረስ ጥረቱን እያጠናከረ መሆኑንም ተቋሙ በመካነድሩ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ባደረገው የምግብ ዋስትና ፍላጎት ግምገማ በ2024 15.8 ሚሊዮን ሰዎች የምግብ እርዳታ እንደሚፈልጉ መተንበዩ ይታወሳል።
በብሩክታዊት አሥራት
2024-02-07