አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባለስልጣናት በኢትዮጵያ የተጣለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመጠቀም ሰላማዊ ዜጎችን ማሰራቸውን እንዲያቆሙ ጠይቋል።
መንግሥት አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመጠቀም ጋዜጠኞችን እና ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን በማሰር ዝም ለማሰኘት አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን እየተጠቀመ ነው ሲል አምነስቲ ከሷል።
የኢትዮጵያ መንግሥት አዋጁን በመጠቀም መሰረታዊ መብቶችን የመጣስ አሮጌ ሲል የጠራውን መንገድ መከተሉን እንዲያቆም ሲልም አሳስቧል።
በአማራ ክልል በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች የተገደሉ ንፁሃን ዜጎችን አስመልክቶ መረጃዎች እንደደረሱት ገልፆ ጉዳዩን እየመረመረ መሆኑን አስታውቋል።
በናርዶስ ታምራት
2024-02-20