ሀገሬ ቲቪ

በአዲስ አበባ 20 አዳዲስ የኤሌክትሪክ ሚኒባሶች የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ።

በአዲስ አበባ 20 አዳዲስ የኤሌክትሪክ ሚኒባሶች የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ።

የስምሪት መስመራቸው ከቦሌ-በሚሊኒየም-በስቴድዮም-ሜክሲኮ (ቡናና ሻይ) እና ከቦሌ-በሚሊኒየም-በጊዮን_ፒያሳ አገልግሎት ቢሮው አስጀምሯል፡፡

የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎትን በዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪኖች መሰጠቱ የህዝብ ትራንስፖርት አቅርቦቱን ከማሻሻሉ በተጨማሪ የበካይ ጋዝ ልቀት በመቀነስና ከተማዋን የሚመጥንና ውብ ገፅታ ከመገንባት አንፃር የሚኖረው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከጊዜ ወደ ጊዜ በአለም አቀፍ ደረጃ ዋጋው እየናረ የመጣውን የተሽከርካሪ ነዳጅ በኤሌትሪክ ሃይል እንዲተካ በማድረግ ለነዳጅ የሚወጣውን የውጭ ምንዛሬ የማዳን ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

በብሩክታዊት አሥራት
2024-02-20