ኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ ድርሻ በአክሲዮን ገበያው አማካኝነት ለሕዝብ ሊሸጥ ነው።
የኢትዮጵያ መንግሥት የኢትዮ ቴሌኮምን 10 በመቶ ድርሻን በአክሲዮን ገበያው የመሸጥ ፍላጎት እንዳለው አስታውቋል ሲል ሮይተርስ አስነብቧል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የቦርድ አባላት ጋር በመከሩበት ወቅት 10 በመቶ የሚሆነውን የኢትዮ ቴሌኮም ድርሻ በአክሲዮን ገበያው አማካኝነት ለህዝብ ወደ ገበያ እንደሚያቀቡ አስታውቀዋል።
ከዚህ ቀደም መንግሥት 5 በመቶ የሚሆነውን የኩባንያውን ድርሻ ለመሸጥ አቅዶ እንደነበር ይታወሳል።
በይስሃቅ አበበ
2024-02-21