
የ6ኛው የአፍሪካ የሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና የልዑካን ቡድን ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ ቦሌ አለም አቀፍ አዉሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚ/ር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረ/ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በአቀባበል መርሃ_ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ በእንግድነት መገኘታቸውን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡
በይገደብ ዓባይ
2024-02-27