ሀገሬ ቲቪ

የአውሮፓ ሀገራት ወደ ዩክሬን ጦራቸውን የመላክ ፍላጎት እንደሌላቸው አስታወቁ።

የአውሮፓ ሀገራት ወደ ዩክሬን ጦራቸውን የመላክ ፍላጎት እንደሌላቸው አስታወቁ።

በዩክሬን ጉዳይ ለመምከር በፓሪስ የተገናኙት የአውሮፓ ሀገራት መሪዎች ጦራቸውን ወደ ዩክሬን እንደማይልኩ አስታውቀዋል።

የጀርመኑ ቻንስለር ኦላፍ ሾልዝ መሪዎቹ በፓሪስ ባደረጉት ምክክር ላይ መሪዎቹ ኬየቭን ለማገዝ ወታደር የመላክ ፍላጎት አልነበራቸውም ሲሉ ገልፀዋል ሲል አርቲ ኒውስ አስነብቧል።

ሩሲያ በበኩሏ አንድም የአውሮፓ ሀገር ጦር በዩክሬን ቢዋጋ ቀጥተኛ ጦርነት ይነሳል ብላለች።

ከቀናት በፊት የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ዩክሬን ጦርነቱን እንድታሸንፍ አውሮፓውያን ጦራቸውን ወደ ዩክሬን መላክ አለባት ለዚህ ፈረንሳይ ዝግጁ ናት ማለታቸው ይታወሳል።

በማህሌት አማረ
2024-02-28