ሀገሬ ቲቪ

በጋዛ ከ500 ሺ በላይ ዜጎች በከፋ ረሃብ ደጃፍ ላይ እንደሚገኙ የተባበሩት መንግስታት አስታወቀ።

በጋዛ ከ500 ሺ በላይ ዜጎች በከፋ ረሃብ ደጃፍ ላይ እንደሚገኙ የተባበሩት መንግስታት አስታወቀ።

ይህ የተባበሩት መንግስታት ማስጠንቀቂያ የተሰማው የእስራዔል ጦር በጋዛ ምግብ እየጠበቁ በነበሩ ፍልስጤማውያን ላይ ተኩስ መክፈቱን ተከትሎ እንደሆነ አልጄዚራ አስነብቧል።

ድርጅቱ እስራዔል ሥልታዊ በሆነ መንገድ ሰብአዊ ድጋፍ ለጋዛ ዜጎች እንዳይደርስ እያደረገች ነው ሲል ከሷል።

እስካሁን እስራኤል በጋዛ እያደረገችው ባለው ጦርነት ወደ 30 ሺ የሚጠጉ ፍልጤማውያን ለሞት ተዳርገውል።

በወንድማገኝ አበበ
2024-02-28