ሀገሬ ቲቪ

በግላስኮ የአለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና የተሳተፈው የአትሌቲክስ ቡድን አዲስ አበባ ገባ።

በግላስኮ የአለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና የተሳተፈው የአትሌቲክስ ቡድን አዲስ አበባ ገባ።

በ19ኛው የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ላይ ከአፍሪካ አንደኛ ከዓለም አምስተኛ በመሆን ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልኡክ አዲስ አበባ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ አቀባበል ተደርጎለታል።

በአቀባበሉ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚ/ር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረ/ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን ጨምሮ ሌሎች የአትሌቲክስ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

በሻምፒዮናው ኢትዮጵያ በሴቶች 800 ሜትር በፅጌ ዱጉማ እና በሴቶች 1500 ሜትር ፍሬወይኒ ሀይሉ የወርቅ ሜዳሊያን አግኝታለች፡፡

በሴቶች 3000 ሜትር በተደረገ ውድድር ጉዳፍ ፀጋዬ የብር ሜዳሊያ ስታገኝ እንዲሁም በወንዶች 3000 ሜትር ሰለሞን ባረጋ የነሃስ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ ማሞጣታቸው ይታወሳል፡፡

በዚህ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ሁለት ወርቅ አንድ ነሀስ በአንድ ብር በአጠቃላይ በአራት ሜዳሊያዎችን በማግኘት በሜዳልያ ሰንጠረዥ ከአፍሪካ አንደኛ ከአለም አምስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።

በይገደብ ዓባይ
2024-03-05