በቀይ ባህር ሥር የሚገኙ የመረጃ ገመዶች ተበጣጥሰዋል።
በአዉሮፓ እና እሲያ መካከል መረጃዎችን ለመለዋወጥ የሚያግዝ፤ በቀይ ባህር ዉስጥ የተዘረጋ የመረጃ ማስተላለፊያ ገመድ መበጠሱን ተከትሎ በሁለቱ አህጉራት መካከል የነበረዉን የመረጃ ፍሰት እንዳስተጓጎለዉ ቢቢሲ ዘግቧል።
በባህሩ ዉስጥም ከሚገኙት ገመዶች ዉስጥ በርካቶቹ በመበጠሳቸዉ ምክንያት፤ በሁለቱ አህጉራት መካከል ያለዉን የመረጃ ፍሰት በ25 በመቶ እንዳስተጓጎለዉ ተገልጿል።
መቀመጫዉን ሆንግ ኮንግ ያደረገዉ፤ ኤች.ጂ.ሲ ግሎባል ኮሚዩኒኬሽን፤ ከ15 የመረጃ ገመዶች ዉስጥ አራቱ መበጠሳቸዉን የገለፀ ሲሆን፤ ገመዶቹ በምን ምክንያት እንደተበጠሱ የተረጋገጠ ነገር እንደሌለ ተነግሯል።
በናርዶስ ታምራት
2024-03-06