ሀገሬ ቲቪ

የሄይቲዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣናቸዉን ለቀቁ

የሄይቲዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤሪኤል ሄንሪ ስልጣናቸዉን መልቀቃቸዉን ቢቢሲ ዘግቧል።

በሀገሪቱ የሚገኙ አማፂ ቡድኖች ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፈቃዳቸዉ ስልጣናቸዉን የማይለቁ ከሆነ የእርስ በርስ ጦርነት እንደሚያስነሱ መዛታቸዉ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ የቀጠናዉ ሀገራት፤ በሄይቲ ለተከሰተዉ አለመረጋጋት መፍትሄ ለመፈለግ ትናንት በጃማይካ የተሰበሰቡ ሲሆን፤ በዚህ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤሪኤል ሄንሪ ስልጣን ለመልቀቅ መስማማታቸዉ ተነግሯል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አለም አቀፍ ሰላም አስከባሪ ኃይል በሀገራቸዉ ላመሰማራት ከኬንያ ጋር ለመነጋገር ጎረቤት ሀገር በመጡበት ወቅት፤ አማጺ ቡድኖቹ ዋና ከተማዋን መቆጣጠራቸዉን ተከትሎ፤ ወደ ሀገራቸዉ መመለስ ሳይችሉ ቀርተዋል።

በበላይሁን ፍስሐ
2024-03-12