ሀገሬ ቲቪ

በስለላ የተጠረጠረ ደቡብ ኮሪያዊ በሩሲያ በቁጥጥር ስር ዋለ

አንድ የደቡብ ኮሪያ ዜጋ በስለላ ወንጀል ተጠርጥሮ በሩሲያ በቁጥጥር ስር መዋሉን የሴኡል ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማስታወቁን ዩፒአይ ዘግቧል።

ታሳሪው ፓርክ ዋን ሱን የሚባል ሲሆን ለምርመራ ወደ ሞስኮ መላኩ ተነግሯል።

ሩሲያ ደቡብ ኮሪያዊን በስላላ ወንጀል ጠርጥራ ስትይዝ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ተመላክቷል።

ደቡብ ኮሪያ፣ ሩሲያ ከዩክሬን ጋር በምታደርገው ጦርነት ምክንያት ምዕራባውያን የሚጥሉትን ማዕቀብ በመደገፏ በሩሲያ "ወዳጅ ያልሆነች" ሀገር ተብላ ተፈርጃለች።

በብሩክታዊት አሥራት
2024-03-12