ሀገሬ ቲቪ

ለሶሪያ ሰብአዊ እርዳታ ያስፈልጋታል - የተባበሩት መንግስታት ድርጅት

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሶሪያ ልዩ መልዕክተኛ ጌየር ኦቶ ፔደርሰን፤ በሀገሪቱ ከ16 ሚሊዮን በላይ ሰዎች እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው አስታወቁ፡፡

ልዩ መልዕክተኛው ቁጥሩ በሶሪያ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ እጅግ ከፍተኛው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በሶሪያ መንግሥት እና በተቃዋሚ ኃይሎች መካከል የሚደረጉ ውይይቶች ፍሬያማ እንዲሆኑ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ገንቢ ሚና እንዲጫወት ጌየር ኦቶ ፔደርሰን አሳስበዋል፡፡

አሁን ላይ በሶሪያ 23.2 ሚሊዮን ህዝብ እንደሚኖር የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (OCHA) መረጃ ያመላክታል፡፡

በናርዶስ ታምራት
2024-03-16