ሀገሬ ቲቪ

እስራኤል በራፋህ ጥቃት መጀመር የሚያስችላትን የውጊያ እቅድ አጸደቀች

በራፋህ ውጊያ ለመጀመር እና ሰላማዊ ሰዎችን ለማስወጣት የሚያስችለው እቅድ መጽደቁን የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ ገልጿል።

እስራኤል በራፋህ ጥቃት ለመክፈት ወታደራዊ ዝግጅት ብታደርግም ንጹሃንን ወደሌላ ስፍራ ለማዘዋወር ያደረገችውን ቅድመ ዝግጅት እንደማይጠቁም ተነግሯል።

በራፋህ ንጹሃንን በማስወጣት በሃማስ ታጣቂዎች ላይ ዘመቻ መክፈታቸው አይቀሬ መሆኑን ያነሱት የኔታንያሁ አስተዳደር አሜሪካን ጨምሮ አለም አቀፍ ነቀፌታ እየገጠማቸው ይገኛል።

በዚህም የአሜሪካ ባለስልጣናት ኔታኒያሁ ንጹሃን ፍልስጤማውያንን መጠበቅ ካልቻሉ ከስልጣን እንዲነሱ እየጠየቁ እንደሚገኙ ሬውተርስ ዘግቧል።

በብሩክታዊት አሥራት
2024-03-16