ሀገሬ ቲቪ

እስራኤል በሶሪያ ላይ በፈፀመችው ጥቃት ከ40 በላይ ሰዎች ተገደሉ።

በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ በደረሰ የአየር ጥቃት ቢያንስ 42 ሰዎች መሞታቸውን ዘገባዎች አመልክተዋል።

የሶሪያ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው የእስራኤል አውሮፕላኖች በአሌፖ ገጠራማ አካባቢዎች በርካታ ቦታዎችን ኢላማ አድርገዋል።

መቀመጫውን በእንግሊዝ ያደረገው የክትትል ቡድን የሂዝቦላህ ታጣቂ ቡድን የጦር መሳሪያ ማከማቻ መመታቱን ተናግሯል።

እስራኤል በሶሪያ ከፈፀመቻቸው ጥቃቶች ውስጥ አሁን ላይ በአንድ ጊዜ የሞቱት የሶሪያ ወታደሮች ቁጥር ከፍተኛው መሆኑን ጠቁሟል ቡድኑ።

ሁለት የደህንነት ምንጮችን ጠቅሶ የሮይተርስ የዜና ወኪል እንደገለጸው ከሟቾቹ መካከል 5 የሂዝቦላህ ተዋጊዎች እንደሚገኙበት ገልጿል።

እስራኤል ጥቃቱን በተመለከተ ዜናው እስከተጠናከረበት ሰዓት ድረስ ያለችው ነገር አለመኖሩን ቢቢሲ ዘግቧል።

በብሩክታዊት አሥራት
2024-03-29