
የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይብ ኤርዶጋን በግንቦት 9 ወደ አሜሪካ እንደሚያቀኑ አንድ የሀገሪቱ የደህንነት ባለሥልጣን ተናግረዋል።
ባለስልጣኑ ስለጉብኝቱ ተጨማሪ መረጃ ባይሰጡም በቅርቡ የተፈቀደውን የአሜሪካ ኤፍ-16 ተዋጊ አውሮፕላኖችን መግዛትን ጨምሮ የእስራኤልና ሐማስን ጦርነት አእንዲሁም የመከላከያ ኢንዱስትሪ ትብብር ላይ ሊወያዩ እንደሚችሉ ተንታኞች ተናግረዋል።
ከሰሞኑ የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን እና የመከላከያ ሚኒስትር ያሳር ጉለርም ከአሜሪካ ልዑካን ጋር መገናኘታቸው ይታወሳል።
በአንካራ የሚገኘው ዋሽንግተንም ሆነ የአሜሪካ ኤምባሲ በጉብኝቱ ላይ የሰጡት አስተያየት የለም ሲል ሬውተርስ ዘግቧል።
የፕሬዝዳንቱ የአሁኑ ጉብኝት ከ2019 በኃላ የመጀመሪያው መሆኑ ተነግሯል።
በብሩክታዊት አሥራት
2024-03-29