ሀገሬ ቲቪ

ታይዋን በርዕደ መሬት ተመታች።

ታይዋን በ25 ዓመታት ውስጥ ትልቁ ነው በተባለለት ርዕደ መሬት ተመታች።

በርዕደ መሬት መለኪያ 7.2 በተለካው ርዕደ መሬት ምስራቃዊ የባህር ዳርቻ ከተማዋን አጥቅቷል።

እስካሁን 4 ሰዎች መሞታቸው የተሰማ ሲሆን 97 ሰዎች ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸው አርቲ ኒውስ አስነብቧል።

ርዕደ መሬቱ የመሬት ናዳን ጨምሮ ሕንፃዎችን እና መኖሪያ ቤቶችን ወደ ፍርስራሽነት ቀይሯቸዋል።

በሳምሶን ገድሉ
0024-04-03