ሀገሬ ቲቪ

ጆ ባይደን እስራዔልን ወቀሱ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እስራዔል የተራድዖ ሰራተኞችን ከጥቃት እየጠበቀች አይደለችም አሉ።

ይህ የባይደን አስተያየት እስራዔል በጋዛ በመንቀሳቀስ ላይ የነበሩ 7 የተራድዖ ሰራተኞችን በአየር ጥቃት ከገደለች በኋላ ነው።

በቅርቡ የጆ ባይደን አስተዳደር ለእስራዔል አዲስ ወታደራዊ ድጋፍን ማፅደቁ ይታወሳል። እንግሊዝ፣ አሜሪካ፣ ካናዳ፣ አውስትራሊያ እና ፖላንድ በሰኞ ጥቃት ዜጎቻቸውን ካጡ በኋላ እስራኤል ጥቃቱ በገለልተኛ አካል ምርመራ ለማድረግ ቃል ገብታለች።

በማህሌት አማረ
2024-04-03