ሀገሬ ቲቪ

አትሌት ትዕግስት አሰፋ በለንደን ማራቶን ተጠባቂዋ አትሌት ሆናለች፡፡

ለመጀመሪያ ግዜ በለንደን ማራቶን የምትሳተፈው አትሌት ትዕግስት አሰፋ የውድድሩ ተጠባቂዋ አትሌት ሆናለች፡፡

የፊታችን እሁድ በሚካሄደው ተጠባቂው የ2024 የለንደን ማራቶን ውድድር ላይ የምትሳተፈው አትሌት ትዕግስት አሰፋ በውድድሩ ከሚጠበቁ አትሌቶች መካከል ቀዳሚዋ ሆናለች፡፡

ከወራቶች በፊት የበርሊንን ማራቶን 2፡11፡53 በመግባት የዓለም ክብረወሰን ባለቤት የሆነችው ትዕግስት አሰፋ ከአዘጋጆቹ ጋር በነበራት ቆይታ እንደተናገረችው “ለንደን የመጣሁት ለማሸነፍ ነው” ስትል ተናግራለች፡፡

አያይዛ ትዕግስት እንደገለጸችው የቦታውን ክብረወሰን እቅድ እንዳላትም ጨምራ ገልጻለች፡፡

በይገደብ ዓባይ
2024-04-19