ሀገሬ ቲቪ

የካናዳ መንግሥት ዜጎቹ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች እንዳይጓዙ ማስጠንቀቂያ ሰጠ

የካናዳ መንግሥት በኢትዮጵያ የፀጥታ ችግር አለባቸው ባላቸው የተለያዩ አካባቢዎች ጉዞ እንዳያደርጉ ማስጠንቀቂያ ሰጠ።

በዚህም በትግራይ፣ በአማራ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ፣ በሲዳማ ክልሎች አንዳንድ አካባቢዎች መንቀሳቀስ እንደሌለባቸው አስታውቋል።

ከኤርትራ ድንበር 10 ኪሎ ሜትር፣ ከሶማሊያና ኬኒያ የሚያዋስኑ ድንበሮች 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ዙሪያ ዜጎች እንዳይንቀሳቀሱ ሲል የጉዞ መረጃዎችን በሚሰጥበት መካነ ድሩ አስፍሯል።

በማህሌት አማረ
2024-04-22