ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተለያዩ ምክንያቶች ተደጋጋሚ የኃይል አቅርቦት መቋረጥ እንዳጋጠመው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡
ይህንን የአቅርቦት መቋረጥ ድግግሞሽ ለመቀነስ እየሰራለሁ ነው ያለው አገልግሎቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ33 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የኤሌክትሪክ መስመር ቅድመ ጥገና እንደተከናወነ አስታውቋል፡፡
2 ሺህ 45 አዳዲስ ትራንስፈርመሮች መተከላቸውንም አገልግሎቱ እወቁልኝ ብሏል፡፡
ከወራት በፊት በተመሳሳይ ጊዜ በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ለሰዓታት የዘለቅ የኤሌክትሪክ አቅርቦት መቋረጥ አጋጥሞ እንደነበር ይታወሳል፡፡
በእሱባለው ጋሻው
2024-04-23