ሀገሬ ቲቪ

የቻይናው ዘኒት ስቲል ኩባንያ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ገብቶ ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እንዳለው ገለፀ።

የቻይናው ዘኒት ስቲል ኩባንያ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ገብቶ ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እንዳለው ገለፀ።

ኩባንያው ይህን ያስታወቀው ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አክሊሉ ጋር በመከረበት ወቅት ነው።

መቀመጫውን በቻይና ሀገር ቻንግዙ ግዛት ያደረገው ኩባንያው ወደ ስራ ሲገባ በቦሌ ለሚ ኢንደስትሪ ፓርክ ከ150 ሚሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስት እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።

በቀጣይ ደግሞ በሌሎች ኢንዱስትሪ ፓርኮችና የድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጣና ከ100 ሄክታር በላይ የለማ መሬት በመውሰድ ወደ ስራ የሚገባ መሆኑን በውይይቱ ገልጿል፡፡

ከዚህ ቀደም የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድራቸው በተለያዩ የኢንደስትሪ ፓርኮች ውስጥ የውጭ ኩባንያዎች ለመሰማራት እቅድ እንዳላቸው ማስታወቃቸው ይታወሳል።

ኩባንያው በቻይና ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ብረታ ብረቶችንና የኤሌክትሪክ መሳሪያዎችን በማምረት ይታወቃል።

በብሩክታዊት አሥራት
2024-04-24