ሀገሬ ቲቪ

‘‘ከ 50,000 በላይ ዜጎች ተፈናቅለዋል’’ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት።

በኢትዮጵያ በሰሜኑ ክፍል በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ከ50 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎች መፈናቀላቸውን፤ የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ጉዳዩች ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) በመካነ ድሩ አስፍሯል፡፡

በራያ አላማጣ፣ ዛታ እና ኦፍላ ወረዳዎች በተቀሰቀሰው የጸጥታ ችግር፣ ወደ ሰሜን ወሎ እና ዋግኽምራ ብሔረሰብ ዞኖች የተፈናቀሉ ዜጎች ያሉበትን ኹኔታ አሳሳቢ እንደሆነ ተቋሙ ሰኞ ባወጣው ሪፖርት ላይ ጠቁሟል።

በተለይ ሴቶች እና ሕፃናት በሕይወት ለመቆየት ሰፊ ሰብአዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ብሏል ኦቻ በሪፖርቱ፡፡

በናርዶስ ታምራት
2024-04-24