በ2016 ዓ.ም 6 ወራት ብቻ በመንገድ ትራፊክ አደጋ ምክንያት 1358 ሰዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ ከ 1 ቢሊዮን ብር በላይ የሚሆን ንብረት መወደሙ ተነገረ።
ይህ የተነገረው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የመንገድ ደኅንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት የ3ኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻፀም በገመገመበት ወቅት ነው።
ይሁን እንጂ የትራፊክ አደጋን 27.46 በመቶ መቀነስ መቻሉን የመንገድ ደህንነት መድን ፈንድ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አባሶ ገለጸዋል።
በወንድማገኝ አበበ
2024-04-24