ሀገሬ ቲቪ

የመብራት ኃይል አቅርቦት ኢንዱስትሪዎችን እየፈተነ ነው

በአዳማ የመብራት ኃይል አቅርቦት ችግር ለኢንዱስትሪዎች ፈተና መሆኑ ተገለፀ።

በከተማዋ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች የመብራት ኃይል አቅርቦት ችግር እየፈተናቸው መሆኑን ቢገልጹም የከተማዋ አመራሮችም ጉዳዩ ከአቅማቸው በላይ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢንዱስትሪና ማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በአዳማ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎችን በጎበኙበት ወቅት መፍትሄ በማፈላለጉ በኩል እንዲያግዛቸው የከተማዋ አመራሮች ጠይቀዋል፡፡

የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት ማነስ፣ የመለዋወጫና ግብአት እጥረት፣ በቂ የብድር አቅርቦት አለመኖርም በጉድለት የተነሱ ጉዳዮች ናቸው፡፡

በናርዶስ ታምራት
2024-04-24