ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

ኢትዮጵያ ቡና እና መቻል አንድ አንድ ተጨዋች ተካፈሉ

ሁለቱ ክለቦች ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን የይገባኛል ጥያቄን በማቅረብ ሲከራከሩ ከቆዩ በኋላ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን በተጫዋቾቹ ላይ የአራት ወራት ዕገዳ እና የ200 መቶ ሺህ ብር ቅጣት በማስተላለፍ በመጨረሻም በመቻል እንዲጫወቱ በሚል መወሰኑ ይታወሳል።

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 1

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የክረምት የዝውውር መስኮት መከፈትን ተከትሎ በመቻል ቆይታ የነበራቸው የመስመር ተከላካዩ አለምብርሀን ይግዛው እና አማካዩ አብዱልከሪም ወርቁ ውላቸው መጠናቀቁን ተከትሎ በመቻል ውል ሲያራዝሙ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ቡና ደግሞ ሌላ ፊርማ በማኖራቸው ለሁለት ክለብ መፈረማቸውን ተከትሎ መነጋገሪያ ጉዳይ እንደነበር ይታወሳል።
ይህንን ጉዳይ ተከትሎ ሁለቱም ክለቦች ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን የይገባኛል ጥያቄን በማቅረብ ሲከራከሩ ከቆዩ በኋላ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን በተጫዋቾቹ ላይ የአራት ወራት ዕገዳ እና የ200 መቶ ሺህ ብር ቅጣት በማስተላለፍ በመጨረሻም በመቻል እንዲጫወቱ በሚል መወሰኑ ይታወሳል።
የፌዴሬሽኑን ውሳኔ ተከትሎ ከመቻል ጋር የቅጣት ጊዜያቸው እስኪጠናቀቅ ልምምድ ሲሰሩ የቆዩት አለምብርሀን እና አብዱልከሪም ሁለቱም የአዲስ አበባ ከተማ ክለብ በመሆናቸው ጉድለታቸውን ለመሙላት ባደረጉት ንግግር ሁለቱም በጋራ በመስማማታቸው አንድ አንድ ተጫዋች ተከፋፍለዋል ስለሆነም የመስመር ተከላካዩ አለምብርሀን ይግዛው በመቻል እንዲቀጥል አማካዩ አብዱልከሪም ወርቁ ደግሞ ለኢትዮጵያ ቡና እንዲጫወት ተወስኗል።

አጋራ

YouTube

አማEN