ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ ቀጣዩ የማንችስተር ዩናይትድ አሠልጣኝ ሊሆኑ ነው!
ማንችስተር ዩናይትድ አርጀንቲናዊውን አሠልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ ቀጣዩ የክለቡ አሠልጣኝ አድርጎ ለመሾም ከጫፍ መድረሱ ተሰምቷል።
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 2

ማንችስተር ዩናይትድ አርጀንቲናዊውን አሠልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ ቀጣዩ የክለቡ አሠልጣኝ አድርጎ ለመሾም ከጫፍ መድረሱ ተሰምቷል።
ዘ አትሌቲክ ከደቂቃዎች በፊት ይዞት በወጣው መረጃ እንግሊዛዊውን አሠልጣኝ ማይክል ካሪክ እንደሚያሰናብት የሚጠበቀው ማንችስተር ዩናይትድ አሁን የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን እያሰለጠኑ የሚገኙትን ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ ለመሾም ሂደቱን እያጠናቀቀ እንደሚገኝ ዘግቧል።
የቀድሞው የቶተንሃም ፣ የፒኤስጂ እና ቼልሲ አሠልጣኝ የነበሩት ፖቼቲኖ የግል ጥቅማጥቅም ችግር ይፈጥራል ተብሎ የማይጠበቅ ሲሆን ነገር ግን ከአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያላቸውን ውል ለማፍረስ ማንችስተር ዩናይትድ 7.4 ሚሊየን ፓውንድ እንደሚከፍል ይጠበቃል።
ስምምነቱ ከተጠናቀቀ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ ሙሉ የአሠልጣኝ ቡድን አባሎቻቸውን ይዘው መምጣት ስለሚፈልጉ ማንችስተር ዩናይትድ ተጨማሪ የካሳ ክፍያዎችን ለመክፈል እንደሚገደደ ዘ አትሌቲክ አስነብቧል።
ከአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን ጋር እስከ 2030 የሚያቆይ ኮንትራት ያላቸው ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ ማንችስተር ዩናይትድን የማሠልጠን የረዥም ጊዜ ፍላጎት እንደነበራቸው የሚታወቅ ሲሆን አሁን ይሄንን እድል ለማግኘት የተቃረቡ ይመስላሉ።
ማንችስተር ዩናይትድ በአዲሱ የውድድር ዘመን ካደረጋቸው 10 የሊግ ጨዋታዎች አንዱን ብቻ በማሸነፍ 18ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ሲሆን ይህም ከ 1986 በኋላ እጅግ መጥፎ አጀማመር ነው።
ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ በ 2016 ከሰር አሌክስ ፈርጉሰን ጋር በለንደን የምሳ ግብዣ ካደረጉ በኋላ ጆዜ ሞሪኒሆ ቦታውን ከመያዛቸው አስቀድሞ አዲሱ የኦልድትራፎርድ አለቃ ይሆናሉ የሚሉ ሪፖርቶች ይወጡ ነበር።
በተመሳሳይ በ2022 የማንችስተር ዩናይትድ አመራሮች ከቴን ሃግ ጋር ለመቀጠል ከመወሰናቸው በፊት ማውሪሲዮ ፖቼቲኖን ማነጋገራቸው ይታወሳል።
