ወደ ዋናው ይዘት ዝለል

በቫሌንሺያ ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰን ለሚሰብር 18 ሚሊየን ብር ሽልማት ተዘጋጅቷል

ታህሳስ 6 ቀን 2026 (እ.ኤ.አ.) የሚካሄደው የቫሌንሺያ ማራቶን አዘጋጆች፣ ከትሪኒዳድ አልፎንሶ ፋውንዴሽን በተዘጋጀ የ1 ሚሊዮን ዩሮ ጉርሻ በመታገዝ የሴቶች ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰንን ለመስበር በግልጽ እያለሙ መሆኑን አስታወቁ።

ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 2

በወንዶች በኩል የነበረው የክብረ ወሰን ተስፋ ዮሚፍ ቀጄልቻ በጉዳት ምክንያት ከውድድሩ ራሱን ማግለሉን ተከትሎ ላይሳካ ይችላል ተብሏል። በሴቶች ምድብ ግን ተስፉ አለዉ ተብሏል።

👉የዓለም ክብረ ወሰን ኢላማዎች እና ጉርሻ

👉የውድድር ቀን፦ ታህሳስ 6 ቀን 2026 (እ.ኤ.አ.)

👉የዓለም ክብረ ወሰን ሽልማት፦ ክብረ ወሰን ለሚሰበር እያንዳንዱ የዓለም ክብረ ወሰን (በወንዶች ወይም በሴቶች) 1 ሚሊዮን ዩሮ የሚሰጥ ሲሆን፣ ይህንን ሽልማት የሚያገኙ አትሌቶች መደበኛውን የውድድሩን የአሸናፊነት እና የቦታው ክብረ ወሰን ሽልማት አያገኙም (በዚህ ሽልማት ይተካል)።

👉የሴቶች ክብረ ወሰን፦ 2:09:56 (በ2024ቱ የቺካጎ ማራቶን በሩት ቼፕንጌቲች የተመዘገበ)።

👉የወንዶች ክብረ ወሰን፦ 1:59:30 (በ2026ቱ የለንደን ማራቶን በሳባስቲያን ሳዌ የተመዘገበ)።

👉 ነባር የቫሌንሺያ ማራቶን ክብረ ወሰኖች፦ 2:01:48 (በወንዶች፣ ሲሳይ ለማ፣ 2023) እና 2:14:00 (በሴቶች፣ ጆይሲሊን ጄፕኮስጌይ፣ 2025)።

በግል ምርጥ ሰዓታቸው መሰረት በቫሌንሲያ ማራቶን የሚሳተፉ 10ሩ ፈጣን አትሌቶች፦

🇪🇹 ፎትየን ተስፋይ (2:10:51)
🇰🇪 አግነስ ጀቤት ንጌቲች (የመጀመሪያ ውድድር)
🇰🇪 ጆይሲሊን ጄፕኮስጌይ (2:14:00)
🇪🇹 ሱቱሜ ከበደ (2:15:55)
🇹🇿 ማግዳሌና ሻውሪ (2:18:03)
🇰🇪 ሊሊያን ካሳይት ሬንገሩክ (2:19:35)
🇪🇹 አበሩ አያና (2:20:20)
🇪🇸 ላውራ ሉዌንጎ (2:22:31)
🇫🇷 መቅደስ ወልዱ (2:23:13)
🇬🇧 ሮዝ ሃርቪ (2:23:21)

አጋራ

YouTube

አማEN