“የድሮን ቀረፃ አሳሳቢ ነው” ሚኬል አርቴታ!
የአርሰናሉ አሠልጣኝ ሚኬል አርቴታ የማንችስተር ዩናይትድ ልምምድ በድሮን መቀረፁ ከተሰማ በኋላ ጉዳዩ አሳሳቢ መሆኑን ተናገረ።
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 1
ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ ማንችስተር ዩናይትድን ከተረከቡ በኋላ በዚህ ሳምንት ያደረጉት የመጀመሪያ ልምምድ በአንድ የድሮን አብራሪ ተቀርጾ ዩቲዩብ ገፅ ላይ ተለቆ ነበር። አብራሪው በጉዳዩ ዙሪያ ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን የ 12 ደቂቃው ቀረጻም ከገፁ ላይ እንዲጠፋ ተደርጓል።
ባለፈው ወር አርሰናል በካራባኦ ካፕ አራተኛ ዙር በፍሊትውድ ተሸንፎ በወጣበት ጨዋታ አንድ ድሮን ከሜዳው በላይ በመብረሩ ጨዋታው ለስምንት ደቂቃዎች ተቋርጦ ነበር።
በዩናይትድ የካሪንግተን የልምምድ ማዕከል ስለተፈጠረው ክስተት የተጠየቁት አርቴታ “በጣም ጥንቃቄ የሚሻ ጉዳይ ነው። እኛም ከፍሊትውድ ጋር በነበረን ጨዋታ ተመሳሳይ ክስተት አጋጥሞን ነበር። በዓለም ዙሪያ እየሆነ ያለውንም እያያችሁ ነው” ብሏል።።
አርቴታ አክሎም ”መፍትሔው ምን እንደሆነ በግልጽ አላውቅም ነገር ግን ቴክኖሎጂ እያደገ ነው። ወደ ሥርዓቶች ሰርጎ የመግባት አቅም በጣም በፈጣን ሁኔታ እያደገ በመሆኑ ለዚህ ጉዳይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን ሆኖም ግን እውነቱን ለመናገር መፍትሔው ይህ ነው ብዬ መናገር አልችልም” ሲል ተደምጧል።
ከዚህ ቀደም በፒኤስጂ በተጫዋችነት አብረው ባሳለፉት ጊዜ ፖቼቲኖን እንደ አባት እንደሚመለከተው የገለፀው የ44 ዓመቱ አርቴታ ዩናይትድ እሑድ ዕለት ወደ ሊቨርፑል ከማቅናቱ በፊት ከቀድሞ የቡድን አጋሩ ጋር መነጋገሩን ይፋ አድርጓል።
አርቴታ “ከፖቼቲኖ ጋር ተነጋግሬያለሁ፤ በጣም ደስተኛ እና ከፊቱ ለሚጠብቀው ሥራ ከፍተኛ ተነሳሽነት ያለው ይመስላል። መልካም ዕድል እመኝለታለሁ” ብሏል።
