የቀድሞ የአርሰናል አሠልጣኝ ማንችስተር ዩናይትድን ተቀላቀለ!
ማንቸስተር ዩናይትድ የቀድሞውን የአርሰናል የአካል ብቃት አሰልጣኝ ሳም ዊልሰንን የዋናው ቡድን የአካል ብቃት አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል።
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 1
ዊልሰን በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ማንቸስተር ዩናይትድን የተቀላቀለ ሲሆን ክለቡ እስካሁን ይፋዊ መግለጫ አላወጣም።
በትናንትናው ዕለት ማንቸስተር ዩናይትድ በአንፊልድ በሊቨርፑል 4-0 በተሸነፈበት እና የማውሪሲዮ ፖቸቲኖ የዩናይትድ አሰልጣኝነት ዘመን እጅግ በከፋ ሁኔታ በጀመረበት ምሽት ሳም ዊልሰን ከአሠልጣኝ ቡድን አባላቱ ጋር ታይቷል።
ይህ ሹመት የመጣው ዊልሰን ለ 12 ዓመታት ያገለገለበትን የሰሜን ለንደኑን ክለብ አርሰናል ከለቀቀ ከአራት ወራት በኋላ ነው።
ዊልሰን በአርሰናል አካዳሚ ውስጥ በተለያዩ የስራ ኃላፊነቶች ካሳለፈ በኋላ የዋናው ቡድን ዋና የአካል ብቃት አሰልጣኝ ለመሆን በቅቶ ነበር።
ኤምሬትስን ከለቀቀ በኋላ ወደ ፓርማ በማቅናት የቀድሞ የአርሰናል ባልደረባው ከሆነው ካርሎስ ኩዌስታ ጋር አብሮ የሰራ ሲሆን አሰልጣኙ በመስከረም ወር መጨረሻ የሴሪ አውን ክለብ እስከለቀቀበት ጊዜ ድረስ በጣሊያን ቆይታ አድርጓል።
ከሌሎች በርካታ የቀድሞ ባልደረቦቹ በተለየ መልኩ የዊልሰን ከአርሰናል መልቀቅ ውሳኔው የመጣው በግል ፍላጎቱ እንደነበር ተገልጿል።
በአርሰናል መቆየት ቢችልም በሌላ ክለብ ከፍ ያለ የኃላፊነት ቦታ ለመያዝ ሲል መልቀቅን እንደመረጠ ሲገለፅ በወቅቱ ወደ ዩቬንቱስ ሊያመራ እንደሚችል በስፋት ተያይዞ ሲነሳ ነበር።
