አድካሚ ጉዞ እና ልምምድ ባልሰራንበት ሜዳ መጫዎታችን ውጤት እንድናጣ አድርጎናል:- አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሀየ
ለ2028 ኦሊምፒክ የአፍሪካ ምድብ የመጀመሪያ ማጣሪያውን ከሞሮኮ ጋር ያደረገው የኢትዮጵያ ከ23 አመህ በታች ብሄራዊ ቡድን በድምር ውጤት 6 ለ 3 ተሸንፎ ከውድድሩ ተሰናብቷል።
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ

ጨዋታውን መግለጫ የሰጠጡት የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሀየ ክለቦች ከነበረባቸው ተደራራቢ ውድድር አንፃር ጥሪ ያደረጉላቸውን ተጨዋቾች በሙሉ አለማግኝታቸውን ተናግረዋል።
ከዕድሜ ጋር በተያያዘ እስከ 2028 ድረስ ከ23 አመት በላይ ሊሆኑ የሚችሉ እና ጥሩ መጫወት የሚችሉትን መቀነሳቸውንም ገልፀዋል። ከድሬዳዋ ከተማ እና ከመቻል ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ማድረጋቸውን የተናገሩት አሰልጣኙ ከዝግጅት ጊዜው ይልቅ በጉዞ ላይ ያሳለፉት ቀናት ብዙ መሆኑን ተናግረዋል።
ለሞሮኮው የመልስ ጨዋታ መከላከል ላይ የነበራቸውን ክፍተት ለመሙላት መስራታቸውን ገልፀው ነገር በሞሮኮ በተጫወቱበት ስታዲየም መጠነኛ እንግልት እንደገጠማቸው ተናግረዋል።
ጨዋታው በተደረገበት ስታዲየም ልምምድ ሳይሰሩ በመግባታቸው እና ተጫዋቾቹ በማያውቁት ስታዲየም መጫወታቸው እንዲሁም የነበረው ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ ለውጤታ ማጣታቸው ትልቁ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል።
