“የዴቪድ ራያ ጉዳት አሳሳቢ አይደለም” ሜኬል አርቴታ
በ11ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል ከሜዳው ውጪ ከኒውካስል ሁለት አቻ በተለያየበት ጨዋታ ግብ ጠባቂው ዴቪድ ራያ ጉዳይ ገጥሞት ተቀይሮ መውጣቱ ይታወሳል።
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 2
በሠዓቱ የተጨዋቹ ጉዳት ከባድ ሊሆን ይችላል ቢባልም አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ዛሬ በሰጠው መግልጫ የስፔናዊው ግብ ጠባቂ ጉዳት ያን ያክል አሳሳቢ እንዳልሆን ይፋ አድርጓል።
ተጨዋቹ ነገ ተጨማሪ የህክምና ምርመራ እንደሚደረግለት የተናገርው አርቴታ አርሰናል በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ከቦሩሲያ ዶርትሙንድ በሚያደርገው ጨዋታ ግን እንደማይሰለፍ ተናግሯል።
ያለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ምርጡ ግብ ጠባቂ የገጠመው ጉዳት ያን ያክል እንደተፈራው አሳሳቢ አለመሆኑ ለአርሰናል ትልቁ ዜናም ሆኖለታል።
የመድፍኞቹ የመከላክል ጥንካሬ ዋናው ሰው እና ማጥቃቱን የሚያስጀመርው ዴቪድ ራያ እሱ በተሰለፈባቸው ጨዋታዎች አርሰናል በፈለገው የጨዋታ መንገድ ነጥቦችን በልበ ሙሉነት የሚሰበስብ ሲሆን በተለይ የኋለኛው ክፍል በቀላሉ እንዳይጋለጥ በማድርግ ወሳኙ የኋላ ደጀን በመሆን ለዩነት ፈጣሪ መሆኑን በተደጋጋሚ አስመስክሯል።
አርሰናል በውውድር ዓመቱ ለጀመረ ጠንካራ ጉዞ እና ሊያሳካው ለሚፈልገው ውጤት ሁነኛው ግብ ጠባቂ ዴቪድ ራያ በጉዳቱ ጥቂት ጨውታዎች ሊልፉት ቢችሉም ለወሳኝ መርሀግብሮች ግን የመድርሰ ዕድሉ ሰፊ ሆኗል።
