“ሴኔጋል ወይስ ሞሮኮ” ካስ የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮኑን ዛሬ ይፋ ያደርጋል
በሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር ሞሮኮ ተካሂዶ በነበረው የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜ ሴኔጋል ሞሮኮን አሸንፋ ዋንጫውን ማንሳቷ የሚታወስ ነው።
ዜና ክፍል · · 1 ደቂቃ ንባብ · 1
ነግር ግን በፍጻሜው ዕለት በተፈጠረው ውዝግብ ምከንያት ጨዋታው ለ17 ደቂቃ ተቋርጦ የነበር ሲሆን ከተቋረጠበት በቀጠለው የአህጉሩ ትልቁ ዋንጫ ሴኔጋል 1 ለ 0 ማሸነፏም ይታወሳል።
የሞሮኮ እግር ኳስ ፌደሬሽንም የተፈጠረውን ጉዳይ መነሻ በማድረግ ለካፍ ይግባኝ ሰሚ ቦርድ ቅሬታውን በማስገባቱ ጉዳዩ ሲመረመር ቆይቷል።
ጉዳዩን ሲመረምር የቆየው አፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን (ካፍ) ይግባኝ ሰሚ ቦርድ በአፍሪካ ዋንጫ ደንብ ቁጥር አንቀጽ 84 መሰረት በሞሮኮ የአፍሪካ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ላይ የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ተሸናፊ ሆኖ እንዲመዘገብ እና በተቃራኒው ሞሮኮ ሜዳ ላይ ብትሸነፍም ዋንጫው እንደሚገባት ወሳኔ አሳልፎ ነበር።
በዚህም መሠረት የጨዋታው ውጤት የሞሮኮ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን 3 ለ 0 አሸናፊ ሆኖ እንዲመዘግብ እና ሴኔጋልን ጥፋተኛ በማድረግ ዋንጫው ለሞሮኮ ካፍ መወሰኑ የሚታወስ ነው።
ነገር ግን ሴኔጋል የካፍን ውሳኔ በመቃወም ጉዳዩን ለዓለም አቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት ካስ ይግባኝ ጠይቃ ውጤቱን ስትጠብቅ ቆይታለች።
ባለፉት ወራት ጉዳዩን ሲመረምር የቆየው ካስ ዛሬ በይፋ የ2025 አፍሪካ ዋንጫ ለማን እንደሚሰጥ የሚያሳውቅ ይሆናል።
ለመሆኑ በእናንት እይታ የአፍሪካ ዋንጫው ለማን ይገባል? ለሞሮኮ ወይስ ለሴኔጋል? ሀሳባችሁን በኮሜንት አጋሩን!
#digitalhagerie #AFCON2025 #CAS #sengal #morocco
